News

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡በጦርነቱ የተጎዱ የመሠረተ ልማት ተቋማትን በመገንባት ኮሚሽኑ ኀላፊነቱን ይወጣል ነው ያሉት። 
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ይልቃል ሽፈራው ባለፉት 50 ዓመታት ኮሚሽኑ በሰውሠራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱ ችግሮች የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት እያቋቋመና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል። አሁንም ለችግር የተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ኮሚሽኑ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን እንደሚወጣ አቶ ይልቃል ተናግረዋል። 
ድጋፍ የተደረላቸው ወገኖች የቤተክርስቲያኗ የልማት ድርጅት ኃይማኖት ሳይለይ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።